Fana: At a Speed of Life!

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ ከኢ/ር ታከለ ጋር አዲስ አበባ በዲፕሎማሲው ዘርፍ ባለት ሚና ላይ ያተኮረ ውይይት አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ጋር ተወያይተዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እና ምክትል ከንቲባው አዲስ አበባ ከተማ በዲፕሎማሲው ዘርፍ ባለት ሚና ላይ ያተኮረ ውይይት ማድረጋቸውን ምክትል ከንቲባው በፌስቡክ ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

እንዲሁም አዲስ አበባ ለሁሉም ምቹ እና ተወዳጅ ዋና ከተማ እንድትሆን በሚሰሩ ስራዎች ላይ በማተኮር መወያየታቸው ነው የተነገረው፡፡

የአፍሪካ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችና 33ኛው የመሪዎች ጉባኤ ከጥር 28 እስከ የካቲት 2 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ይጠበቃል፡፡

ጉባኤው የተዋጣለት እንዲሆን ከዚህ ቀደም ከተካሄዱት ጉባኤዎች በተሻለ መልኩ ለማካሄድ መንግስት ፍላጎት እንዳለው እና ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.