Fana: At a Speed of Life!

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ ከዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት ዳይሬክተር ጄኔራል ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት ዳይሬክተር ጄኔራል አንቶኒዮ ማኑኤል ጋር በትብብር በሚሰሩ ጉዳዮች ዙሪያ በስልክ ተወያዩ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ በውይይታቸው ወቅት ድርጅቱ ከመካከለኛው ምስራቅ ወደ አገራቸው ለሚመለሱ ኢትዮጵያዊያን ለሚያደርገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ድጋፉ ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነታቸው መሆኑንም ገልጸዋል።

ድርጅቱ የግንኙነት ጽህፈት ቤቱን ኢትዮጵያን ሳያማክር አሁን ካለበት ወደ ጎረቤት አገራት ለማዛወር ያሳለፈው ውስኔ አግባብ አለመሆኑን አንስተዋል፡፡

ውሳኔውንም ዳግም እንዲያጤነው አቶ ገዱ በዚህ ወቅት አሳስበዋል።

አብዛኛዎቹ ባለድርሻ አካላት ጽህፈት ቤታቸው ኢትዮጵያ ውስጥ በመሆኑ፤ IOM የግንኙነት ጽህፈት ቤቱን ኢትዮጵያ ውስጥ ቢያቆይ ለአጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴው አመቺነት ተመራጭ እንደሚሆንም አቶ ገዱ በውይይታቸው አንስተዋል።

አንቶኒ በበኩላቸው ድርጅቱ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ አጠናክሮ ለመቀጠል እንደሚፈልግ ገልጸዋል።

ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍም አጠናክሮ አንደሚቀጥል ቃል ገብተዋል።

የግንኙነት ጽህፈት ቤቱን ወደ ጎረቤት አገራት ለማዛውር ያስተላለፈውን ውሳኔም ዳግም አንደሚያጤነው ዳይሬክተር ጄኔራሩ መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒሰተር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.