Fana: At a Speed of Life!

የውጭ ጫና በኢትዮጵያ ላይ የበረታው የተጀመረውን ለውጥ ለማደናቀፍ ነው – ዑስታዝ ጀማል በሽር

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጫና በኢትዮጵያ ላይ እየበረታ የመጣው አገሪቷን ከያዘችው ትክክለኛ የለውጥና የእድገት አቅጣጫ ለማደናቀፍ መሆኑን የ “ኪንግ ኦፍ ዓባይ ሚዲያ” ባለቤትና የህዳሴ ግድብ ተሟጋች ዑስታዝ ጀማል በሽር ገለጹ ፡፡

ዑስታዝ ጀማል ለኢዜአ እንደነገሩት ፥ በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት በማከናወንና ሁለንተናዊ እድገት በማስመዝገብ የጀመረችው ውጤታማ ሂደት በአንዳንድ ምዕራባውያን አገራት ዘንድ አልተወደደም።

በሁሉም መስኮች ባለፉት ሶስት ዓመታት የተመዘገበው ውጤት እንዲሁም “የተፈጥሮ ሃብቴን በአግባቡ መጠቀም አለብኝ” በሚል የያዘችው አቋም ሁልጊዜም ድህነቷን ለሚመኙት ሁሉ ተቀባይነት አጥቷል ብለዋል ኡስታዝ ጀማል።

በዚህም ከአሜሪካና ከተለያዩ የምእራቡ ዓለም አገራትና ሚዲያዎች ግልጽ የሆነ ጫና እና በጥላቻ የተሞላበት ዘመቻ እየተካሄደባት መሆኑን ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ የምዕራባዊያኑ እርዳታ ጠባቂና ተመፅዋች ሆና እንድትዘልቅ ካላቸው ፍላጎት የተነሳ በኢኮኖሚ ራሷን እንዳትችል ጫናው እየበረታባት መሆኑን አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ ከያዘችው ትክክለኛ የለውጥና የእድገት አቅጣጫ ለማደናቀፍ የውጭው ጫና እየበረታ መጥቱን አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ ሳትጠቀምበት ለዘመናት በዘለቀው የዓባይ ወንዝ ላይ ግድብ ገንብታ ኤሌክትሪክ ለማመንጨት በትክክለኛው ውቅት ላይ መገኘቷም ከተለያዩ አቅጣጫዎች ጫናዎችን አበረትቶባታል ነው ያሉት ኡስታዝ ጀማል።

ኢትዮጵያ የዓባይን ወንዝ ተጠቅማ ሃይል ማመንጨት ከቻለች ሃብት ከመፍጠር ባለፈም ትርጉም ያለው ለውጥ በመሆኑ ከቀርብም ይሁን ከሩቅ ጫና እየፈጠረባት መሆኑን ገልጸዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.