Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ እያደረገ ያለውን ሰብዓዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል አቶ ደመቀ አጥናፉ በኢትዮጵያ አዲሱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም ተወካይ ክላውድ ጂብዳር ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
በወቅቱም የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ ለሚከሰቱ ችግሮች እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች በቀዳሚነት ሰብዓዊ ድጋፍ የሚያደርግ ድርጅት በመሆኑ አቶ ደመቀ አመስግነዋል፡፡
 
መንግስት ለሰብዓዊነት ሲል ግጭት ማቆሙን አስታውሰው ፥ ወደ ትግራይ ክልል በየብስና በአየር ትራንስፖርት ሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲደርስ አመቺ ሁኔታ መፈጠሩን አብራርተዋል፡፡
 
ድርጅቱም በክልሉ ለሚኖረው የሰብዓዊ ዕርዳታ ተግባራት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ፈጣን አገልግሎት እንደሚሰጣቸው አረጋግጠዋል፡፡
 
አዲሱ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ተወካይ ክላውድ ጂብዳር በበኩላቸው ፥ ድርጅታቸው በመላው አገሪቱ እያደረገ ያለውን ሰብዓዊ ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡
 
ክላውድ ጂብዳር የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ የድርጅቱ ተወካይ እና ካንትሪ ዳይሬክተር አድርጎ የሾማቸው መሆኑን የሚገለጽ ደብዳቤ ቅጂ ለፕሮቶኮል ሹሙ ማቅረባቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.