Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት 150 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት የአቅም ግንባታ እና ስልጠና የሚውል 150 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አፀደቀ፡፡

ይህ የገንዘብ ድጋፍ ደረጃውን የጠበቀ ደረጃ ሶስት የባዮሴፍቲ ቤተ ሙከራ ከተሟላ መሳሪያ ጋር ለመገንባት፣ በሁሉም ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች የሚገነባ 15 ደረጃ ሁለት የባዮሴፍቲ ቤተ ሙከራ ከተሟላ መሳሪያ ጋር ለመገንባት፣ በክልል እና በከተማ መስተዳድር የሚገኙ 8 ቤተ ሙከራዎችን ሙሉ መሳሪያ ለማሟላት ይውላል ተብሏል።

እንዲሁም ብሄራዊ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ መከላከያ አስተዳደር ስርዓትን ለማጠናከር፣ ብሄራዊና የክልል እና ከተማ አስተዳደር የመረጃ አያያዝ ስርዓትን ለማጠናከር፣ ለፀረ ተህዋስያን መድኃኒት፣ መቆጣጠሪያ ማዕከላት ለማጠናከር እና ለሰራተኛ የአቅም ግንባታ እንደሚውል የጤና ሚኒስትሩ ዶክተር አሚን አማን ገልፀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.