Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፎች የተጀመሩ ስራዎችን መደገፋን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አመራሮች በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ከተመራው ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ ዓለም ባንክ በተለያዩ ዘርፎች በኢትዮጵያ በተለይም የዲጂታል ፋውንዴሽን ስራ እና በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚከናወኑ ሌሎች ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ ያሳየውን ፍላጎትና ድጋፍ አድንቀዋል።

ሚኒስትሩ የግሉን ዘርፍ በቴሌኮም ዘርፉ ለማሳተፍ ከፖሊሲ አንጻር የነበሩ ስራዎች ከዓለም ባንክ ጋር በቅርበት መሰራታቸውን አስታውሰዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር አህመዲን ሙሀመድ በዲጂታል 2025 ፕሮግራም ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች የዲጂታል አሰራርን ለመዘርጋት የሄደችበትን ርቀት ለልዑካን ቡድኑ አብራርተዋል።

ፕሮግራሙ ወደ ትግበራ ለመግባት ከልዩ ልዩ አካላት ጋር ድጋፍና ትብብር በሚያስፈልጉ ጉዳዮች ላይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተቀናጅቶ ለመስራት የልየታ ስራ ዝግጅት በማጠናቀቅ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ተወካይ ኦስማን ዲዮን በበኩላቸው የዓም ባንክ በኢትዮጵያ የሚያደርጋቸውን ድጋፎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅሰው፥ በተለያዩ ሀገራት ካገኟቸው ተሞክሮዎች አንጻር የዲጂታል አጀንዳ ትግብራን ለማረጋገጥ የተሻለ ጅምር እንዳለ ተናግረዋል።

የዓለም ባንክ ግብርና፣ ቱሪዝም፣ ከተማና ትራንስፖርት እንዲሁም ሌሎች ዘርፎች በቴክኖሎጂና ዲጂታይዜሽን ለማዘመን በኢትዮጵያ የሚደረገውን ጥረት ከመንግስት ጎን በመሆን እንደሚደግፍም ቃል ገብተዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የጀመራቸውን የተለያዩ ፕሮግራሞች ውጤታማ ለማድረግ የዓለም ባንክ የቴክኖሎጂ አማካሪዎች ቡድን ለመመደብ ዝግጁ እንደሆነ መግለጻቸውንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.