Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ ጨምሮ ለስድስት ሃገራት ለግብርና ዘርፉ የሚውል የ60 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም ባንክ የቦርድ ዳይሬክተሮች የአየር ንብረት ለውጥ ስጋት ያንዣበበበትን የግብርና ዘርፍ ለመደገፍ እና ለማጠናከር ኢትዮጵያን ጨምሮ ለስድስት አፍሪካ ሀገራት የ60 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ፡፡

ድጋፉ በአውሮፓውያኑ 2019 ባካሄደው የአየር ንብረት ጉባዔ ላይ በመከረበት ወቅት የገባውን ቃል ለማሳካት መሆኑን ነው በመግለጫው የገለጸው፡፡

በወቅቱ ጉባዔው ዓለም አቀፍ ትብብር የታየበትና ዓለም አቀፍ ተቋማት የምግብ ዋስትና ላይ ያተኮረ ጥናት እንዲያካሄዱ እንዲሁም በግብርና ላይ የተመሰረቱ ገጠራማ አካባቢዎችን ለመደገፍ ከግብርና ጋር የተያያዙ ምርምሮችን ለማካሄድ ያተኮረ እንደነበር አስታውሷል፡፡

የዓለም ባንክ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንዲሁም ግብርናውን ለመደገፍ ሳይንስና የተለያዩ ፈጠራዎችን መጠቀም የሚያበረታታ ሲሆን ከዚህ ቀደም የአየር ንብረት ተጽዕኖ የሚያስከትለውን የምግብ ዋስትና ስጋት ለመቅረፍ በአህጉሪቷ የባለብዙ ወገን ስምምነት መደረሱንም በመግለጫው አስታውሷል፡፡

በዚህም ባንኩ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሴኔጋል፣ ለጋና፣ ለማሊ፣ ለኬንያ እና ለዛምቢያ ድጋፍ ማድረጉን ነው ያስታወቀው፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.