Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ባንክ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በቅርበት መስራቱን  እንደሚቀጥል አረጋገጠ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  የዓለም ባንክ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በቅርበት መስራቱን  እንደሚቀጥል አረጋገጠ።

ባንኩ ዛሬ ከሰዓት በኋላ  ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት እያከናወነ ያለውን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በፋይናንስ መደገፉን እንደሚቀጥል አስታውቋል።

ባንኩ በመግለጫው ከፈረንጆቹ ሀምሌ ወር 2020 እስከ ሰኔ ወር 2023 ድረስ ኢትዮጵያ ለምታከናውናቸው የልማት ስራዎች የሚሰጠው  አጠቃላይ የፋይናነስ ድጋፍ 2 ነጥብ 9 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚደርስ አመልክቷል።

የበጀት ድጋፍን ጨምሮ ባንኩ የፋይናስ ድጋፍ የሚያደረግባቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች ለዓለም ባንክ ስራ አስፈፃሚ ቦርድ ለውይይት እየቀረቡ የመፅደቃቸው ጉዳይም መደበኛ አካሄድን ተከትሎ እየተከናወነ መሆኑን አብሮ ገልጿል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.