Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጀመራልየዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮሎምቢያ ካሊ የሚካሄደው የዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ሲጀምር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ ርቀቶች ይሳተፋሉ፡፡

በዚህም መሰረት ምሽት 12: 00 ሰዓት የወንዶች 1500 ሜትር  የማጣሪያ ውድድር የሚደረግ ሲሆን፥  ምሽት 12:30 ደግሞ የሴቶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ውድድር ይካሄዳል፡፡

የፍፃሜ ውድድሮች ሌሊት የሚደረጉ ሲሆን ከምሽቱ 7: 00  የሴቶች 3 ሺህ ሜትር ፍፃሜ እንዲሁም ሌሊት 7: 55 የወንዶች 5 ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር ይደረጋሉ፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 1 : 08 የሴቶች 800 ሜትር ማጣሪያ ውድድር የሚካሄድ መሆኑን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.