Fana: At a Speed of Life!

የዓለም የምግብ ፕሮግራም የትምህርት ቤት ምገባን እንዲደግፍ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም የምግብ ፕሮግራም የትምህርት ቤት ምገባን እንዲደግፍ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጠየቁ፡፡

ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ክላውዴ ጂቢዳር  ጋር ተወያይተዋል።

በትምህርት ዘርፉ የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ሪፎርሞች መጀመራቸውን ጠቅሰው÷ በትምህርት ቤት ምገባ ዙሪያም እየተሰሩ ስላሉ ስራዎች አብራርተዋል፡፡

የዓለም የምግብ ፕሮግራም በአዲስ መልክ የተጀመረውን የትምህርት ቤት የምገባ ፕሮግራም በሁሉም ክልሎች እንዲስፋፋ ድጋፍ እንዲያደርግም ጠይቀዋል።

የዓለም የምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ተቋሙ ከትምህርት ቤት ምገባ በተጨማሪ በርካታ የምግብ እና የቴክኒክ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ገልፀው÷ ለውጤታማቱ የመንግስት ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን አክለዋል።

በትምህርቱ ዘርፍ የተጀመረው ስራም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጻቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የትምህርት ቤት ምገባ በአዲስ አበባ እና በአንዳንድ ክልሎች እየተተገበረ እንደሚገኝም ተገልጿል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.