Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ጤና ድርጅት ለኮሮና ቫይረስ በ18 ወራት ውስጥ ክትባት እንደሚያዘጋጅ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት በ18 ወራት ውስጥ ለኮሮና ቫይረስ ክትባት ለማግኘት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም እንደገለጹት፥ የኮሮና ቫይረስን የመጀመሪያ ክትባት በ18 ወራት ጊዜ ውስጥ ማግኘት ይቻላል።

ዳይሬክተሩ አያይዘውም አሁን ላይ የሚገኙትን መሳሪያዎች በመጠቀም መስራት ይገባል ብለዋል።

ተመራማሪዎች፣ የግል ኩባንያዎች እና ሃገራት ለቫይረሱ ክትባት ለማዘጋጀት ጥረት እያደረጉ ይገኛል።

በብሪታኒያ በአንድ የምርምር ቡድን እየተደረገ ያለው ምርምርም እመርታ እያሳየ መሆኑ ተገልጿል።

በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሺህ በላይ መድረሱን መረጃዎች ያመላክታሉ።

ከዚህ ባለፈም የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር 40 ሺህ በላይ የደረሰ ሲሆን፥ ቫይረሱ በርካታ ሃገራትንም አዳርሷል።

ምንጭ፦ ሲ ጂ ቲ ኤን

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.