Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ጤና ድርጅት አመታዊ ጉባኤውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም የጤና ድርጅት አመታዊ ጉባኤ በቪዲዮ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።

ጉባዔው በዋናነት አባል ሀገራቱ ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ የሚያተኩር ነው ተብሏል።

በጉባዔው መክፈቻ ላይ የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ሃገራቸው ቫይረሱን ለመቆጣጠር አበረታች ስራ መስራቷን ጠቅሰው፥ አስፈላጊው ግምገማ ቫይረሱን መቆጣጠር ከተቻለ በኋላ ይደረጋል ብለዋል።

አያይዘውም ሃገራቸው ቫይረሱን ለመከላከል የሚውል 2 ቢሊየን ዶላር እንደምትለግስ ቃል ገብተዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በበኩላቸው ዓለም ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ነርሶች እና አዋላጆች ያስፈልጓታል ብለዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ የጤና ባለሙያዎች ድርጅቱ እያደረገ ያለውን ጥረት እንዲቀላቀሉም ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ፦ አልጀዚራ እና ቢቢሲ

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.