Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ጤና ድርጅት ኮቪድ የመጣው ከውሃን ቤተ ሙከራ ሳይሆን ከእንስሳት መሆኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮና ቫይረስ መነሻ ከውሃን ቤተ ሙከራ ሳይሆን ከእንስሳት መሆኑን በጥናቱ አረጋገጠ፡፡

የድርጅቱ ልዑክ ቻይና በመገኘት የኮሮና ቫይረስን መነሻ ሲያጠና መቆየቱ ይታወቃል፡፡

የልዑክ ቡድኑ መሪ ፒተር ቤን ኢምባረክ መነሻውን ለማወቅ ተጨማሪ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸውም ገልጸዋል፡፡

ጥናቱን የድርጅቱ ልዑክ እና ቻይና የጤና ኮሚሽን በጋራ ማጥናታቸው ነው የተነገረው፡፡

ውሃን በቻይና ምዕራባዊ ሁቤ አውራጃ የምትገኘ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ኮሮና ቫይረስ የተገኘባት ከተማ መሆኗ ይታወሳል፡፡

ባለሙያዎች ወረርሽኙ ወደ ሰዎች ከመሰራጨቱ በፊት ከእንስሳ እንደመጣ ቢያምኑም እንዴት ሊከሰት እንደቻለ እርግጠኞች አይደሉም ተብሏል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.