Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን አስመልክቶ የአውሮፓ ሀገራትን አስጠነቀቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን አስመልክቶ የአውሮፓ ሀገራትን አስጠነቀቀ፡፡

ድርጅቱ በመላው አውሮፓ ሀገራት እየተመዘገበ ያለው በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እንደማንቂያ ደውል ሆኖ ሊያገለግሉ ይገባልም ነው ያለው፡፡

የአለም ጤና ድርጅት የቀጠናው ዳይሬክተር በኮፐንሃገን ባደረጉት ንግግር እንዳሉትም ÷ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከግማሽ በላይ በሆኑ የአውሮፓ ሀገራት በእጥፍ አድጓል ብለዋል ፡፡

በዚህም ባለፈው ሳምንት ብቻ 300 ሺህ አዲስ በቫይረሱ ተያዙ ሰዎች በመላው አውሮፓ ሪፖርት የተደረጉ ሲሆን÷ ሳምንታዊ ሪፖርቶችም በመጋቢት ወር ከተመዘገበው ከፍተኛ ቁጥር አልፏል ነው የተባለው፡፡

ምንም እንኳን እነዚህ ቁጥሮች የበለጠ አጠቃላይ ምርመራውን የሚያንፀባርቁ ቢሆኑም አሳሳቢ የሆነውን የስርጭት መጠን ያሳያል ብለዋል ፡፡

ይህን ተከትሎም ከፊታችን በጣም ከባድ የሆነ ሁኔታ እየተከሰተ ነው ማለታቸውም ነው የተነገረው፡፡

በአለም ጤና ድርጅት መረጃ መሰረት ወረርሽኙ ከተከሰተ ጀምሮ በመላው አውሮፓ 5 ሚሊየን ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 228 ሺህ በላይ የሚሆኑት ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ
#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.