Fana: At a Speed of Life!

የዓባይ ጉዳይ በትምህርት ስርዓት ተካቶ ሊቀርብ ይገባል የኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር ጠቆመ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር የአባይ ጉዳይ በኢትዮጵያ ትምህርት ስርዓት ውስጥ ተካቶ ቢቀርብ ግንዛቤ ለተተኪው ትውልዱ ከመፍጠር አንፃር ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው አስገነዘበ፡፡
የኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር ቀደም ባሉት ዘመናት እነ ጸጋዬ ገብረ መድህን፣ አቤ ጉበኛ፣ አያልነህ ሙላቱ፣ ሰይፉ መታፈሪያ ፍሬው፣ ኃይሉ ገብረ ዮሃንስ (ገሞራው)፣ ሙሉጌታ ተስፋዬ፣ ኮሎኔል ሞገስ ሀብቱ እና የመሳሰሉት የመድረክ ሰዎች፣ ገጣሚያን እና ባለቅኔዎች በዓባይ ላይ ብዙ ቢሉም ፀፀትንና የተለያዩ ስሜቶችን ከማንፀባረቅ ባለፈ ትውልድ ለመቅረፅ የነበራቸው ፋይዳ እምብዛም እንደነበረ ያወሳል፡፡
አሁን ላይ ግን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጀመር የዓባይ ዘመን ብዕሮች ከሃዘን፣ ከቁጭትና ከእንጉርጉሮ ተላቀው በተስፋ፣ በጥቅም፣ በሕብረት እና በአንድነት ጉዳዮች ላይ በሚያተኩሩ ለተተኪው ትውልድ ተስፋን የሚያሰንቁ የጥበብ ስራዎች መተካታቸውን ማህበሩ ያነሳል፡፡
በቀጣይም በዓባይ ጉዳይ ላይ የሚሰሩ የጥበብ ስራዎች ፋይዳ እንዲኖራቸው በትምህርት ስርዓት ውስጥ ተካተው ሊቀርቡ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡
ይህም በዓባይ ጉዳይ ላይ ለማስረዳት የሚችል በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ትውልድ ለመፍጠር እንደሚረዳ መመላከቱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር ከግድቡ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጋር በመተባበር አንጋፋና ወጣት ደራሲያን የተሳተፉበት ሁለት የጽሁፍ ስራዎች መታተማቸውን ጠቅሷል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.