Fana: At a Speed of Life!

የዘማች ቤተሰቦች የኢትዮጵያ የምንግዜም ባለውለታዎች ናቸው- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ99 የዘማች ቤተሰቦች የመኖሪያ ቤት ቁልፍ እና ከ1 ሺህ 450 በላይ ለሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች ደግሞ የገና በአልን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ስጦታዎችን አበረከተ፡፡

በቁልፍ ርክክቡና ስጦታው ፕሮግራም ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የዘማች ቤተሰቦች ውድ ህይወታቸውንና የተለያዩ አካላቸውን ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት የሰጡ የጀግና ልጆች ቤተሰቦች በመሆናቸው የኢትዮጵያን ሉአላዊነትና የግዛት አንድነት ስናስብ ሁሌም የምናስባቸው ባለውለታዎች ናቸው ብለዋል፡፡

አገሪቷም ባላት ሃብት ሁሉ ቅድሚያ በመስጠት የምትደግፈውና የምታበረታታው እነዚሁኑ ጅግኖችና ቤተሰቦቻቸውን ነው ብለዋል፡፡

የአካል መቁሰልና ሞት በማንኛውም ተራ ምክንያት ሊከሰት የሚችል ክስተት መሆኑን ያነሱት ከንቲባዋ፥ ለአገር ሉአላዊነት መስዋዕት መሆንና የአገርን ክብር ለማስጠበቅ ዋጋ መክፈል ዘላለማዊ ኩራት ነው ብለዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የተሳተፉ የዲያስፖራ አባላትም ለነዚህ የአገር ባለውለታዎች ለማክበርና ከጎናችሁ ነን ለማለት ላደረጉት ድጋፍ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ለዘማች ቤተሰቦች የሚያደርገውን ድጋፍም አጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለፃቸውን ከአስተዳደሩ ፕረስ ሰክረተሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.