Fana: At a Speed of Life!

የዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዕቅድ 61 በመቶ ተከናውኗል

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ3ኛ ዙር ‘ኢትዮጵያን እናልብሳት’ ሀገራዊ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እስካሁን 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ችግ መተከሉ ተገልጿል፡፡
የመርሃ ግብሩ ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ 3ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ዝግጅትና ትግበራን አስመልክቶ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
የኮሚቴው አባል የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሳኒ ረዲ ግንቦት 10 ቀን 2013 ዓ.ም በተጀመረው የችግኝ ተከላ እስከ ሐምሌ 13 ቀን 2013 ድረስ 3 ነጥብ 71 ቢሊዮን ችግኝ መትከል እንደተቻለ ገልጸዋል።
በዚህም እስካሁን የሀገራዊ ዕቅዱን 61 በመቶ ማሳካት መቻሉን ነው የተናገሩት፡፡
የብሔራዊ ኮሚቴው አባል የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በበኩላቸው÷ በዓባይ ተፋሰስ የሚካሄደው የዘንድሮው ግኝኝ ተከላ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ከደለል ለመጠበቅ ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።
በቀጣይም በአንድ ጀምበር በዓባይ ተፋሰስ ውስጥ ችግኝ የመትከል መርሃ ግብር እንደሚከወን መግለፃቸውን ከውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሚተከለው 6 ቢሊየን ችግኝ ውስጥ 75 በመቶው ማለትም 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኝ በዓባይ ተፋስስ እንደሚተከልም ተመላክቷል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.