Fana: At a Speed of Life!

የዩኒሴፍ አመራሮች ተፈናቃዮች ያሉበትን ሁኔታ ለመመልከት ደሴን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የዩኒሴፍ የሀገር ውስጥና የውጭ አመራሮች ተፈናቃዬች ያሉበትን ሁኔታ ለመመልከት ደሴ ተገኝተው ጎብኝተዋል።

ከአመራሮቹ በተጨማሪ የብሪታንያ ልዩ መልዕክተኛ ኒክ ዳየር ተገኝተዋል።

የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ አበበ ገብረመስቀል ለአመራሮቹ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

አቶ አበበ ባደረጉት ንግግርም ሽብርተኛው ህወሓት በከፈተው ጦርነት በርካቶች መፈናቀላቸውን ገልፀው÷ የደሴ ከተማ በ15 መጠለያ ጣቢያዎች ከ15 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች መጠለላቸውን አብራርተዋል።

ሰብዓዊ ድጋፍ በእጅጉ እንደሚያስፈልግም አስምረውበታል።

ለስራ ሃላፊዎቹ የተፈጠረውን መፈናቀል በተመለከተና አጠቃላይ ሁኔታው ምን እንደሚመስል ገለፃ የተደረገላቸው ሲሆን÷ ተፈናቃዮቹ በሚገኙባቸው ጣቢያዎች በመገኘት ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ተወካይ አዴል ኮደር ተፈናቃዬቹን ከጎበኙ በኋላ እጅግ በጣም ልብ በሚነካ አኳኋን መገኘታቸው እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል።

ህፃናት እና እናቶች ለከፋ የምግብ እጥረት መጋለጣቸውን አረጋግጠናል፤ አስቸኳይ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸውም ተመልክተናልም ነው ያሉት።

በዚህም ዩኒሴፍ የቻለውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

ዩኒሴፍን ጨምሮ ሌሎችም ዓለምአቀፍ ረጅ ተቋማት መሰል ድጋፎችን ለሰሜን ወሎ ተፈናቃዬች ለማድረግ አልዘገያችሁም ወይ በሚል ለተነሳላቸው ጥያቄ፣ ተወካይዋ የጦርነት ሁኔታው ውስብስብ በመሆኑ እንጂ አልዘገየንም በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ድጋፍ ስናደርግ ቆይተናል ብለዋል።

በሀብታሙ ተ/ስላሴ እና ስንታየሁ መሀመድ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.