Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ፣ሶማሌ እና የአፋር ክልሎች በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች 53 ሚሊየን ብር እና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ፣ ሶማሌ እና የአፋር ክልሎች በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች 53 ሚሊየን ብርና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ ፡፡
የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው የክልሉ መንግሥት እና ህዝብ በመጀመሪያ ዙር ካደረገው ድጋፍ በተጨማሪ 20 ሚሊየን ብር እና 2 አምቡላንሶችን ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡
ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅትም የትግራይ ህዝብ ለኢትዮጵያ ደማቅ ታሪክ ጽፈው ያለፉ ጀግኖች መፍጠር የቻለ በመሆኑ ክብር ይገባዋል ብለዋል፡፡
በክልሉ ከዚህ ቀደም የተፈጠረውን ያለፈ ታሪክ በመተው የክልሉን ህዝብ ወደ ተሻለ ደረጃ ማድረስ ላይ ሊተኮር እንደሚገባ በመጥቀስ፥ የትግራይን ህዝብ መልሶ ለማቋቋም የተጀመረው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ የአፋር ክልል 13 ሚሊየን በጥሬ ገንዘብ ፣ 1 ሚሊየን 300 ሺህ የሚያወጣ መድሀኒት እንዲሁም 1 አምቡላንስ ድጋፍ አድርጓል፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንደገለጹት በትግራይ ክልል በተፈጠረው የጸጥታ ችግር የአፋርም ክልል ቀጥተኛ ተጎጂ ነው ብለዋል፡፡
በተለይ በህግ ማስከበሩ ወቅት በነበረው ችግር የግብይት ስርአቱ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳረፉን በማሳያነት ጠቅሰው ትግራይን ወደነበረችበት መመለስ ብቻ ሳይሆን ከዚያም በላይ ከፍ ለማድረግ እንሰራለንም ነው ያሉት፡፡
እንዲሁም የሶማሌ ክልል በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
በዚህ ወቅትም ለትግራይ ህዝብ ታላቅ አክብሮት አለኝ ያሉት የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በቀጣይም የህዝብ ለህዝብ ትስስር ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራና የተደረገው ድጋፍ ቀጣይነት እንደሚኖረውም አስረድተዋል፡፡
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ የክልሎቹ ህዝብ እና መንግሥት ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.