Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሚገኘውን ዕምቅ የተፈጥሮ ሀብት ለመጠቀም ዘላቂ ሰላምን ማስፈን ያስፈልጋል- ዶ/ር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 7፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በተፈጥሮ ሀብት የታደለ በመሆኑ ይህንን ሀብት ለመጠቀምና ለመበልፀግ ዘላቂ ሰላምን ማስፈን ይገባል ሲሉ ደቡብ ምዕራብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ ተናግረዋል።
ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞና ሸካ ዞኞች ተገኝተው የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፤ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋርም ተወያይተዋል
በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ በተደረገ ውይይትም ክልሉ ዕምቅ ሀብት ያለው በተፈጥሮ ሀብትም የታደለ አካባቢ ቢሆንም ያለውን ሀብት መጠቀም ሳንችል ቆይተናል ነው ያሉት
አክለውም ክልሉ ያለውን ፀጋ ለመጠቀም አስቀድሞ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ሁሉም መረባረብ እንደሚኖርበት አሳስበዋል
ጦር ተማዘን ያገኘነው አንዳች ነገር የለም ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ፥ ከትናንሽ ቁርሾዎች ወጥተን አካባቢውን ለማሳደግ በጋራ መቆም አለብን ነው ያሉት
በተስፋየ ምሬሳ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.