Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የባህል ፌስቲቫልና ኤግዚቢሽን ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የባህል ፌስቲቫልና ኤግዚቢሽን በቦንጋ ከተማ ዛሬ በይፋ ተከፈተ፡፡
 
በመክፈቻ መርሐ ግበሩ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስነ-ጥበብና ስራ ዕድል ፈጠራ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ነፊሳ አልማሃድ፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ፣ የክልሉዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ጸጋዬ ማሞ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
 
ከሁሉም ዞኖች የተወጣጡ የባህል ቡድኖች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶችም በመርሐ ግብሩ ተሳትፈዋል፡፡
 
የባህል ፌስቲቫልና ኤግዚቢሽኑ “ባህላችን ለዘለቂ ሰላማችን እና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ቃል ነው የሚካሄደው፡፡
 
የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ብላቴ ÷ የባህል ፌስቲቫልና ኤግዚቢሽኑ በክልሉ የሚገኙ 13 ብሔረሰቦች ባህላቸውን በማስተዋወቅ እንደሚሳተፉ ገልጸዋል።
 
በኤግዚቢሽኑ ባህላዊ አልባሳት፣ ምግብና መጠጦች የሚቀርቡ ሲሆን ፥ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎች በፎቶና በአካል እንደሚጎበኙ ተገልጿል።
 
ለክልሉ የመጀመሪያ የሆነው ፌስቲቫሉ እስከ ግንቦት 27 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ለጎብኝዎች ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ከዳውሮ ዞን ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.