Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የህዝቦች የጋራ የትግል ውጤት ነው – አቶ እርስቱ ይርዳ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ምስረታን በማስመልከት የህዝቦች የጋራ የትግል ውጤት ለሆነው ለአዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝቦች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
አሁን የምንገኝበት ወቅት አገርን ለማዳን ከፍተኛ ተጋድሎ የምናደርግበት ጊዜ በመሆኑ÷ አዲስ የተመሰረተው ክልል ለህልውና ዘመቻው ተጨማሪ አቅም ነው ብለዋል።
የሁለቱም ክልል ህዝብ ከዚህ ቀደሙ ለህልውና ዘመቻው እያደረጉት ያለውን ጥረት በማስቀጠል የጋራ ጠላትን እንዲፋለሙ ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል።
የሁለቱ ክልል ህዝብ የጋራ ማንነት እና እሴት ባለቤት መሆናቸውን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ ለመንግስታዊ አገልግሎት የተዋቀረው አስተዳደራዊ መዋቅር አንድነትን ከማጠናከር አያግደንም ብለዋል፡፡
በጋራ ሰርተን በጋራ እንበለጽጋለን፤ የሁለቱን ክልል ህዝቦች ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር በትኩረት እንሰራለን ማለታቸውን ከደቡብ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ለመላው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት እና ህዝብ እንኳን ለዚህ ታሪካዊ ቀን አደረሳችሁ በማለት ርዕሰ መስተዳድሩ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.