Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ሱዳንን የሽግግር ወቅት መራዘም በበጎ ጎን እንደሚመለከተው የኢትዮጵያ መንግስት አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ሱዳንን የሽግግር ወቅት መራዘም የኢትዮጵያ መንግስት በበጎ ጎን እንሚቀበለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ደቡብ ሱዳን የሽግግር ጊዜውን ለተጨማሪ 24 ወራት አራዝማለች።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ውሳኔው በተጨባጭ ግምገማ ላይ የተመሰረተ ነው ብሎ እንደሚያምን አንስቷል፡፡
የደቡብ ሱዳን መንግስት የተጀመረውን ሰላማዊ ውይይት በተሳካ መልኩ ለማከናወን የምርጫ ጊዜውን በሁለት ዓመታት ለማራዘም ውሳኔ ማሳለፉ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት እስካግባባና የደቡብ ሱዳናውያንን ጥቅም እስካስጠበቀ ድረስ ውሳኔውን በአወንታ እንደሚመለከተው አስታውቋል።
አሁን ያለው የመስማማት እና የመተባበር መንፈስ የሽግግር ጊዜ ቀሪ ተግባራትን ለማከናወን እንደሚረዳም ያለውን ፅኑ እምነት ገልጿል።
ኢትዮጵያ እንደተለመደው የደቡብ ሱዳንን ዘላቂ ሰላምና ብልፅግና ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ከደቡብ ሱዳን ጎን እንደምትቆምም በመግለጫው አመላክቷል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.