Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻር የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻር  በተደረገላቸው ምርመራ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ታውቋል።

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር የተቋቋመ ግብረ ሀይል አባል በቫይረሱ መያዙ ከተረጋገጠ በኋላ ሪክ ማቻር ባደረጉት ምርመራ በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጧል።

የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር የሆኑት የሪክ ማቻር ባለቤት አንጀሊና ተኒናም በቫይረሱ ተይዘዋል ነው የተባለው።

ከዚያም ባለፈ የሪክ ማቻር የግል ጥበቃዎችና ሌሎች የማቻር ቡድን አባላት በቫይረሱ መያዛቸው በምርመራ  ተረጋግጧል።

በደቡብ ሱዳን እስካሁን 282 ሰዎች በኮቪድ -19 ወረርሽኝ የተያዙ ሲሆን 4 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው ማለፉን መረጃዎች ያመላክታሉ ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለፈው ሳምንት በደቡብ ሱዳን በስደተኞች መጠለያ ካምፖች ውስጥ ሁለት ሰዎች በኮሮናቫይረስ በያዛቸውን ተከትሎ በሀገሪቱ ኮቪድ 19 ሰዎች በተጨናነቁባቸው የስደተኞች ካምፖች ውስጥ በፍጥነት ሊሰራጭ ይችላል ሲል ስጋቱን ገልጾ ነበር።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.