Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ፓርላማውን በተኑ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ፓርላማውን ከቅዳሜ ምሽት ጀምሮ በትነዋል፡፡

የፕሬዚዳንቱ እርምጃ በሃገሪቱ የዛሬ ሶስት አመት በተደረሰው የሰላም ስምምነት የተገቡ ቃሎችን ተፈጻሚ ለማድረግ በር ከፋች ነው ተብሎለታል፡፡

ይህም የፓርላማ አባላትንና ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችን ከገዥው ፓርቲ ብቻ ሳይሆን ከተቀናቃኝ ፓርቲዎች ለማካተት የሚያስችል ነው ተብሎለታል፡፡

በሃገሪቱ በፈረንጆቹ 2018 በተደረሰው ስምምነት መሰረት ከፓርላማ አባላቱ መካከል 25 በመቶዎቹ ሪክ ማቻር ከሚመሩት ፓርቲ እንዲሆኑ ይደነግጋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በሃገሪቱ አዲስና ከሁሉም ፓርቲዎች የተዋቀረ መከላከያ ሰራዊት እንዲኖርም ያዛል፡፡

ፕሬዚዳንቱም አዲሱን ፓርላማ ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ቀናት ያዋቅራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከፈረንጆቹ 2013 የጀመረው የደቡብ ሱዳን ግጭት ከ380 ሺህ በላይ ዜጎችን ለህልፈት ሲዳርግ በሚሊየን የሚቆጠሩት ደግሞ ከቤት ንብረታቸው እንዲፈናቀሉ ምክንያት መሆኑ ይነገራል፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.