Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ስሪል ራማፎሳ ጠ/ሚ ዐቢይ የአፍሪካ ህብረት ልዑክንን ተቀብለው ስላነጋገሩ ምስጋና አቀረቡ

የአዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር እና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ስሪል ራማፎሳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአፍሪካ ህብረት ልዑክንን ተቀብለው ስላነጋገሩ ምስጋና አቅርበውላቸዋል።

የአፍሪካ ህብረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከአፍሪካ ህብረት ልዑክን ጋር መወያየተቻወን ተከትሎ መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫውም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የቀድሞ የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ፣ የቀድሞው የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ጆኣኪም ቺሳኖና የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ኪጋሌማ ሞትላንቴ ያካተተውን የአፍሪካ ህብረት ልኡክ በትናንትናው እለት ተቀብለው ማነጋገራቸውን አስታውሷል።

በውይይታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለልኡካኑ በትግራይ ክልል እየተካሄደ ስላለው የህግ ማስከበር ዘመቻ ዙሪያ ማብራሪያ መስጠታቸውን አመላክቷል።

እንዲሁም ዘመቻው የህግ ማስከበር መሆኑን እና በአጭር ጊዜ የሚጠናቀቅ መሆኑን፤ በክልሉ የተፈናቀሉ ዜጎችን ሰብዓዊ ድጋፍ የሚየስተባብር እና የሚመለከት ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ መግባቱንም ለልዑካኑ አብራርተዋል ብሏል።

ከዚህ ባለፈም ከቀያቸው የተሰደዱ ተፈናቃዮችን ተቀብሎ ለማቋቋም አራት መቆያዎች መዘጋጀታወንም ለልኡካኑ አብራርተዋል ብሏል የአፍርካ ህብረት በመግለጫው።

የአፍሪካ ህብረት ልዑክኑ ከኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውንም መግለጫው አመላክቷል።

ውይይቱን አስመልክቶም የአፍሪካ ህብረት የወቅቱ ሊቀ መንበር እና የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ስሪል ራማፎሳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአፍሪካ ህብረት ልዑክንን ተቀብለው በማነጋገራቸው ምስጋና አቅርበውላቸዋል።

የአፍሪካ ህብረት በቀጣይም ከኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ ጎን እንደሚሆንም ማረጋገጣቸውንም መግለጫው አመላክቷል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.