Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ለሰራዊቱ በ5ኛ ዙር ከ380 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ክልል ለመከላከያ ሰራዊት ለ5ኛ ዙር ከ380 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉ “ደጀንም ዘማችም ሆነን ኢትዮጵያን እንታደጋለን” በሚል መሪ ቃል የተሰበሰበ ሲሆን÷ ድጋፉ ከ5 ሺህ በላይ ከብቶችን ፣ ምግብና ጥራጥሬዎችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በዝግጅቱ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው ፣ የመከላከያ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ማርታ ሉዊጂ ፣ ጄኔራል መኮንኖች ፣ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሃላፊዎች ፣ የአገር ሽማግሌዎች ፣ የጉራጌ ዞን ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡
አቶ እርስቱ በአገር ህልውና ላይ የሚመጣ ማንኛውንም ጥቃት የመመለከት ጉዳይ ዛሬ ሳይሆን ጥንት አባቶቻችን ተሰባስበው ለአገራቸው ተዋግተውና ደጀን ሆነው ለትውልዱ ማስረከባቸውን አውስተዋል፡፡
አገራችን ለጥቁር ህዝቦች የጀግንነትና አይበገሬነት ምሳሌ ናትና ክልላችን ይህን ለማስቀጠል ለ5ኛ ጊዜ ድጋፍ በማድረግ ኢትዮጵያ የተቃጣባትን ጥቃት መክታ ነፃነቷን አስጠብቃ ወደፊት እንድትሄድ የበኩሉን አስተዋጾኦ ያደርጋልም ብለዋል፡፡
የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ክልል የአንድነት ፣ የፅናት እና የኢትዮጵያዊነት ምሳሌ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የመከላከያ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ማርታ ሉዊጂ ናቸው፡፡
ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡት ሚኒስትር ዲኤታዋ÷ ክልሉ ከዚህ በፊት ለመከላከያ ሠራዊታችን በተከታታይ ለ4 ዙር ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.