Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል መንግስት ለኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የ5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ህዳር 15 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደቡብ ክልል መንግስት ለኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የ5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡
የኦሊምፒክ ኮሚቴውና የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ሃላፊዎች ከደቡብ ክልል አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳንና የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሄለን ደበበን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ በዚሁ ወቅት ÷ የስፖርቱን ዘርፍ በመደገፍ የሀገሪቱን ስምና ዝና ከፍ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
በክልሉም ሆነ እንደ ሀገር የዘርፉ ጥልቅ አቅም እንዳለ ያነሱት አቶ እርስቱ መሰረቱንና የተሳትፎ አይነቱን ማስፋት ላይ ትኩረት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም ስፖርቱን የኢኮኖሚ፣ የሰላም ተምሳሌትና የህዝብ ትስስር ምንጭ ማድረግ እንደሚያስፈልግም አስታውቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ በበኩላቸው÷ እንደ ሀገር በአንዳንንድ የስፖርት አይነቶች ጥሩ ውጤት እየመጣ ቢሆንም የውውድር ስፖርት አይነቶችን በማስፋት ረገድ ብዙ ጥረት እንደሚፈልግ አንስተዋል፡፡
ከአትሌቲክስ በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት ጥሩ ተስፋ እየታየባቸው በሚገኙ የቴኳንዶ፣ የብስክሌትና የቦክስ ስፖርቶች ላይ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባም ነው ያነሱት፡፡
ለተሰጠው ድጋፍ የደቡብ ክልል መንግስትን ያመሰገኑት ዶክተር አሸብር መንግስት እንደ ሌሎቹ የልማት ዘርፎች ሁሉ ለስፖርቱም ትኩረት እንዲሰጥ ጥሪ ማቅረባቸውን ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.