Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ለእጩ ዳኞች ሹመት በመስጠት መደበኛ ጉባኤውን አጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ላለፉት ሁለት ቀናት መደበኛ ጉባኤውን ሲያካሂድ የነበረው የደቡብ ክልል ምክር ቤት በእጩነት ለቀረቡለት 146 ዳኞች ሹመት ሰጥቷል።
ከእነዚህ እጩ ዳኞች ውስጥ 24ቱ ለከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ሲሆን 124ቱ ደግሞ ለወረዳና ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች የተሾሙ ናቸው ተብሏል።
የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ አጎ በዚሁ ወቅት የእጩ ዳኞቹ መሾም ያለውን የዳኞች እጥረት ችግር በመቅረፍ የዳኝነት ስራውን እንደሚያሻሽሉ ተናግረዋል ።
ያም ሆኖ የሴቶች ተሳትፎ አነስተኛ በመሆኑ ትኩረት እንዲሰጠው የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሄለን ደበበ አሳስበዋል።
እጩ ዳኞቹ በህገ መንግስቱ መሰረት ተግባራቸውን ለማከናወን በምክር ቤቱ አባላት ፊት ቃለ መሃላ መፈፀማቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.