Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ የ2014 ዓም የመስቀል በአልን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል ፡-
ለመላው የሀገራችን እና የክልላችን የክርስትና እምነት ተከታዮች እንዲሁም የሀገርን ህልውና ለማስጠበቅ የህይወት መስዋዕትነት እየከፈለ ላለው ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት፣ለልዩ ሀይል ፣ለሚሊሻ አባላት እንኳን ለ2014 ዓም የመስቀል በአል በሰላም አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ።
የመስቀል በአል ብዙዎች በጉጉት የሚጠብቁት እና ከሀይማኖታዊ ፋይዳው ባለፈ ማህበራዊ መስተጋብራችን ይበልጥ የሚጎለብትበት በአል ነው።
መስቀል ለረጅም ጊዜ የተራራቁ የቤተሰብ አባላት እና ወዳጅ ዘመዳሞች ተቀራርበው የሚደጋገፉበት: የተጣሉ የሚታረቁበት: የተቸገረ ወገን የሚደገፍበት: አዲስ ጎጆ የሚመሰረትበትና በአጠቃላይ ለማህበራዊ ችግሮቻቸው መፍትሄ የሚሰጡበት ታላቅ በአል ነው።
መስቀል በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ተቋም /ዩኔስኮ/ በማይዳሰሱ ቅርሶች የተመዘገበ ድንቅ በአልም ነው።
የዘንድሮውን የመስቀል በአል ስናከብር መላው ኢትዮጵያውያን በውስጥ እና በውጭ የሚገኙ ጠላቶቻችን በከፈቱብን ዘመቻ ከፍተኛ ጫና ውስጥ ሆነን ነው።
የሀገርን እድገት የማይፈልገው የህወሃት አሸባሪ ቡድንና ተላላኪዎቹ በከፈቱብን ጦርነትና ጥቃት የብዙዎች ህይወት አልፏል የንብረት ውድመት እና የአካል ጉዳትን ጨምሮ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎቻችን ከሞቀ ቀዬአቸው ተፈናቅለዋል።
ላለፉት 27 አመታት አድራጊ ፈጣሪ የነበረው የትህነግ ቡድን በሰፊው ህዝብ ትግል ስልጣኑን ካጣበት ጊዜ ጀምሮ እኔ ያልመራኋት ሀገር አትኖርም በሚል ቀቢጸ ተስፋ ሀገርን ለማፍረስ ሁሉንም አይነት የሽብር እና የውንብድና ተግባር በመፈጸም ላይ ይገኛል።
በህወሀት የሽብር ቡድን የተከፈተብንን ጦርነት በአስተማማኝ ደረጃ እየመከትን እና ወራሪውን ቡድን በገባበት ቦታ ለመቅበር ጀግኖች ልጆቻችን በጀግነት የህይወት መስዋዕትነት በመክፈል ላይ ናቸው።
የክልላችን ህዝብ ለህልውና ዘመቻው ልጆቹን መርቆ ወደ ግንባር ከመላክ ባለፈ ያለውን እየሰጠ ነው።
አርሶ አደሮች፣ የመንግስት ሰራተኞች ፣የንግዱ ማህበረሰብ ፣ወጣቶች፣ ሴቶች በልዩ ልዩ የሙያ መስክ የተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሀገርን ሉአላዊነት ለማስከበር የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ላይ ናቸው።
ዛሬ የገጠመን ግዙፍ ችግር አሁን ላለንበት ጠንካራ አንድነት ምክንያት ሆኗል።
ይህ የጋራ አንድነት ይበልጥ ጎልብቶ የኢትዮጵያን ትንሳኤ እንዲፋጠን ማድረግ ይኖርብናል።
ጥንት አያት ቅድመ አያቶቻችን በደም እና በአጥንት ያቆዩልንን ሉአላዊት ሀገር በአንድ ጀንበር ለማፍረስ ያለሙ የውስጥ እና የውጭ ሀይሎች ምናልባትም የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ካለመረዳት የመነጨ ነው።
ዛሬ የገጠመንን ፈተና ወደ እድል በመቀየር በተሰማራንበት የስራ መስክ ጠንክሮ በመስራት ልንለውጠው ይገባል።
የውጭ ጫናን መቋቋም የሚያስችል አቅም እስካለን ድረስ ሉአላዊ ክብራችንን ማስጠበቅ ከምንም በላይ ትኩረት በመስጠት ልንሰራ ይገባል።
ይህ እኩይ የጥፋት ሴራ ጠላቶቻችን እንደተመኙት ኢትዮጵያን ያፈራረሰ ሳይሆን የተነጠቅነውን ኢትዮጵያዊነትን ያደመቀ ኢትዮጵያውያንን በህብረት ያቆመ ክስተት ሆኗልና የሀገራችን ትንሳኤያን ማብሰሪያ ሆኖ ያልፋል።
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በአሉ የሰላም፣ የጤና፣ የመተሳሰብ እና የአንድነት በአል እንዲሆን በድጋሚ መልካም ምኞቴን ለመግለጽ እወዳለሁ!!
መልካም በአል!!
May be an image of 1 person and sitting
0
People Reached
26
Engagements
Boost Post
21
4 Comments
1 Share
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.