Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው በካፋ ዞን የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው በካፋ ዞን የተከናወኑ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ላይም የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ  ጥላሁን ከበደን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች መሳተፋቸውን ከክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የስራ ኃላፊዎቹ በዞኑ ባደረጉት ቆይታም በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ የቦቃ ሹታ ምርጥ የቦንጋ በግ ዝርያ ማሻሻያና ማስፋፊያ መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበርን የስራ እንቅስቃሴን ተመልክተዋል።

በደቡብ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የቦንጋ ግብርና ምርምር ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ዘለቀ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፥ አርሶ አደር አሳታፊ በሆነው የቦንጋ በግ ዝርያ ማሻሻያ ፕሮጀክት 15 ማህበራትን ያቀፈ ነው።

በምርምር ማዕከሉ የታቀፉ 2 ሺህ አርሶ አደሮች የሚሳተፉበት ሲሆን፥ የነዚህ ማህበራት ካፒታል ደግሞ ከ20 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ መሆኑንም ዳይሬክተሩ አብራርተዋል።

የምርምር ማዕከሉ የተሻሻሉ ዝርያዎችን እየለየ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት በማሳደግ ላይ ሲሆን፥ ለርቢ የማይሆኑትን ደግሞ  ለስጋ አቅርቦት  እያዘጋጀ መሆኑን አቶ ሙሉቀን ጠቁመዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.