Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን ለሚገኙ ተፈናቃዮች የ10 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል መንግስት በትህነግ ሽብር ቡድን ጥቃት ከወሎ ተፈናቅለው በሰሜን ሸዋ ዞን ለሚገኙ ወገኖች 10 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር የሚገመት የሁለተኛ ዙር የዕለት ምግብ ድጋፍ አደረገ።
በደብረ ብርሀን ከተማ በመገኘት ድጋፉን ያስረከቡት የደቡብ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ÷ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የደቡብ ክልል መንግስትና ህዝብ አጋርነቱን ለመግለጽ ያደረገው ድጋፍ ነው ብለዋል።
የክልሉ መንግስትና ህዝብ ሀገር ለማፍረስ የተነሳውን የትህነግ ሽብር ቡድን ለመመከት ሰራዊት ከመላክ ባሻገር በቅርቡ ከ380 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ማድረጉንም ገልጸዋል።
የትህነግ ሽብር ቡድን እስኪደመሰስ ድጋፋችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አቶ ተፈሪ አባተ አረጋግጠዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የሰሜን ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ወልደ አማኑኤል÷ የደቡብ ክልል ህዝብና መንግስት እያደረገ ላለው ድጋፍ አመስግነው ድጋፉ ሊከፋፍለን የተጋው ትህነግ እንዳልተሳካለት ማሳያ ነው ብለዋል።
በግርማ ነሲቡ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.