Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በሀዲያ ዞን ሻሾጎ ወረዳ ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የደቡብ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በሀዲያ ዞን ሻሾጎ ወረዳ በዶኢሻ ከተማ በ2010 ዓ.ም በዋን ዋሽ አማካኝነት ለከተማው ህዝብ አገልግሎት ይሰጣል በሚል የተቆፈረውን የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ጎብኝተዋል፡፡

የሻሾጎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተስፋዬ እርስቱ ለዶኢሻ ከተማ ህዝብ የንጹህ መጠጥ ውሀ አገልግሎት እንዲሰጥ ከ3 ዓመት በፊት በዋን ዋሽ ፕሮግራም ቁፋሮው ቢጠናቀቅም እስካሁን ድረስ አገልግሎት ሊሰጥ አለመቻሉን ተናግረዋል፡፡

በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ዘርፍ አስተባባሪ እና የትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው የቦኖሻ ሆስፒታል ፕሮጀክት ሳይጠናቀቅ መቆየቱን የክልሉ መንግሥት ተገንዝቧል ብለዋል፡፡

በክልሉ በተያዩ አካባቢዎች ለተጀመሩ ፕሮጀክቶች መጓተት ዋነኛ ምክንያት የኮንትራክተሮች ችግር መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የዶኢሻ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ጋር ተያይዞ የተፈጠረው ችግር በበጀት እጥረት ምክንያት መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በቀጣይ የክልሉ መንግሥት ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል፡፡

የዶኢሻ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ተጠናቆ የመስመር ዝርጋታ ብቻ እንደሚቀረው በጉብኝቱ ወቅት ተጠቁሟል፡፡

ልኡካን ቡድኑ የቦኖሻ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅን የጎበኙ ሲሆን ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ለርክክብ ዝግጁ መሆኑን የደቡብ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.