Fana: At a Speed of Life!

የጤና ባለሙያዎች በከፈሉት መስዋዕትነት በአስከፊ ፍጥነት እየተሰራጨ ከነበረው ወረርሽኝ እኛ ተርፈናል -አቶ ርስቱ ይርዳው

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲየደቡብ ክልል መንግስት አስቸጋሪውን የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ሙያዊ ሀላፊነታቸውንለተወጡ የጤና ባለሙያዎች የእዉቅና ስነ-ስርዓት አዘጋጅቷል።
”ለከፈለችሁላት ዋጋ ኢትዮጵያ ታመሰግናችኋለች ”በሚል መሪ ቃል በሀድያ ዞን ሆሳዕና ከተማ በተዘጋጀው የምስጋና ስነስርዓት ላይ÷ በክልሉ ከሚገኙ ሁሉም አካባቢዎች የጤና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
በአስቸጋሪው ሰዓት ሀላፊነታቸውን ስለተወጡና እየተወጡ ስለሆነ ምስጋና ይገባቸዋል በሚል የክልሉ መንግስት ይህን የምስጋና ስነ-ስርዓት መዘጋጀቱን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል።
ዝግጅቱ በኮሮና ምክንያት የተሠዉ ባለሙያዎችን በጧፍ ማብራት በማሠብ ተጀምሯል።
መዝግጅቱ ላይ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው ተገኝተዋል።
አቶ ርስቱ ይርዳው በፕሮግራሙ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት÷ ክልሉ ባዘጋጀው የጤና ባለሙያዎች የእውቅና ስነስርዓት ላይ ባስተላለፉት የጤና ባለሙያዎች በከፈሉት ዋጋ በኮሮና ምክንያት ይደርስ የነበረው አደጋ ቀንሷል ብለዋል።
ህዝብን በቅንነት ከማገልገል በላይ ክብር የለም ያሉት አቶ ርስቱ የክልሉ መንግሥትም የጤና ባለሙያዎች በሚያስፈልገው ሀሉ ለመደገፍ በቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል።
በጥላሁን ይልማ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
3
Engagements
Boost Post
3
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.