Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ጎንደር ዞን ነዋሪዎች ለሰራዊቱ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናገሩ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ላለፉት አምስት ወራት ለመከላከያ ሰራዊቱ፣ ልዩ ሐይል፣ ፋኖ እና ሚሊሻ ደጀን ከመሆን ባለፈ የስንቅ እና የሞራል ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውን የደብረ ታቦር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
ነዋሪወቹ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት÷ የመንግስት ሰራተኛው፣ ነጋዴው እና የከተማዋ ነዋሪ በዓይነት እና በገንዘብ ድጋፍ ሲያደርጉ ቆይተዋል።
እስካሁን በደብረታቦር ከተማ ብቻ ከ20 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የከተማዋ ከንቲባ ባሻህ እንግዳው ነግረውናል።
ህብረተሰቡ ከገንዘብ ድጋፉ ባለፈ÷ “ትኩስ ምግብ ለሰራዊታችን” በሚል በከተማዋ የሚገኙ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በሳምንት ሁለት ቀን ምሽግ ድረስ በመሄድ ለሰራዊቱ ምግብ እያቀረቡ ይገኛሉ ብለዋል።
የደቡብ ጎንደር ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ እና በጋሸና ግንባር የሎጅስቲክስ አስተባባሪ ጥላሁን ደጀኔ፥ የህወሓት የሽብር ቡድንን ለመታገል የደቡብ ጎንደር ህዝብ ከሰራዊቱ ጋር በመሆን በግንባር ከመፋለም ጀምሮ ደጀን በመሆን የስንቅ እና የሞራል ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በእስካሁኑም ከመንግስት ሰራተኛው፣ ከነጋዴው፣ ከከተማው ነዋሪ እና ከአርሶ አደሩ በአንድ ዓመት ውስጥ 350 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ፥ በአምስት ወራት ብቻ ከ178 ሚሊየን ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ ለመሰብሰብ ተችሏል ነው ያሉት።
እስካሁን 382 ሰንጋ በሬዎች፣ 1 ሺህ 982 ኩንታል የምግብ እህል ድጋፍ መደረጉን የገለጹት አቶ ጥላሁን፥ በዞኑ ከሚገኙ 21 ወረዳዎች ከ5 ሺህ እስከ 20 ሺህ እንጀራ በበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች አማካይነት በየቀኑ ወደ ምሽግ እየደረሰ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
በምንይችል አዘዘው
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.