Fana: At a Speed of Life!

የደብረብርሀን ከተማ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ኮ/ር ታዬ ሀብተጊዮርጊስ በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ‘የደህንነት ስጋት ናቸው’ ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉትን ከእስር በመፍታት የተጠረጠሩት የደብረብርሀን ከተማ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ኮማንደር ታዬ ሀብተጊዮርጊስ በቁጥጥር ስር ዋሉ።
የከተማው ሰላምና ደህንነት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ዳንኤል እሸቴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት÷ የፖሊስ ፅህፈት ቤት ሀላፊው በቁጥጥር ስር የዋሉት ከአሸባሪው ህውሓት ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦችን ያለ ኮማንድ ፖስቱ ፈቃድ ከማቆያ እንዲወጡ አድርገዋል በሚል ነው።
በዚህ ወንጀል የተሳተፉ ሌሎች አመራሮች መኖራቸውን በተመለከተም ከህዝብ ጥቆማዎች እየደረሳቸው እንደሚገኝም አቶ ዳንኤል ገልፀው÷ መረጃውን ለማጥራት እየተሠራ ነውም ብለዋል፡፡

 

ከዚህ ጋር በተያያዘም ከተማ አስተዳደሩ ሁለት የፖሊስ አባላትን በተጨማሪነት በቁጥጥር ስር ማዋሉ አስታውቋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት የፖሊስ አባላት ከሽብር ቡድኑ ህወሓት ጋር ግንኑነት አላቸው ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች ከእስር እንዲፈቱ በማድረጋቸው ነው ተብሏል።

የደብረብረሀን ከተማ አስተዳድር ሰላምና ደህንነት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ዳንኤል እሸቴ በደብረ ብርሀን ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል ሀላፊ ኢንስፔክተር አዲስ ገብረህይወት እና ዋና ሳጅን ሙሉጌታ ጋሻው ናቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

ያስ ሹዬና በእታገኝ መኮንን
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.