Fana: At a Speed of Life!

የደብረ ብርሃን ከተማ ሴቶች የወገን ጦር በህወሓት ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ በመደገፍ ሰልፍ አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደብረ ብርሃን ከተማ ሴቶች አሸባሪ እና ወራሪውን ህወሓት እየተፋለሙ ለሚገኙት መከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ኃይል፣ ፋኖና ሚልሻ ጎን መቆማቸውን ለማሳየት በደብረ ብርሃን ከተማ ሰልፍ አካሂዷል፡፡
 
የድጋፍ ሰልፉ “ጣይቱ ለነፃነት” በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ሲሆን÷በዚህም የወራሪው ህወሓት የመጨረሻ መቀበሪያ የሸዋ ምድር ነው እና ከተማችንን ለስግብግብ ጁንታ አሳልፈን አንሰጥም እና የሽብር ቡድኖቹ ህወሓትና ሸኔ ሀገር የማፍረስ ሴራ በወገን ጦር የተባበረ ክንድ ይከሽፋል የሚሉ መልዕክቶች ተላልፈዋል፡፡
 
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ ÷ ከዚህ በፊት እንቁ ሴቶች በሀገራችን ለነፃነት ተዋድቀዋል፤ ዛሬ እኛም ሀገራችን ለጠላት አሳልፈን እንደማንሰጥ ሊገነዘቡ ይገባል ብለዋል፡፡
 
ሀገራችን የጀግና ሀገር ናትና ከሰራዊቱ ጎን በመሆን ጠላትን በሸዋ ምድር ልንቀብረው ይገባል በማለት የሚያጀግኑ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡
 
የአማራ ክልል የምሁራን መማክርት ጉባኤ የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ኃይማኖት እሸቱ በበኩላቸው ÷ እስካሁን ያለው ይብቃ በማለት ከዚህ በኋላ ለዚህ ወራሪ ጠላት ሴቶችና ወጣቶች ሁሉም በአንድነት ለሀገሩ እንዲዘምት ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
 
ሰራዊቱ ለሀገር እየተዋደቀ ነው፤ እዚህ አጠገባችን የደረሰውን ጠላት ለመቅበር ሁላችሁም ወጣቶች በቅንጅት ተነሱ ሲሉም አሳስበዋል፡፡
 
የሰልፉ ተሳታፊ የሆኑት ወይዘሮ ሚስጥረ በቀለ÷በኢትዮጵያ ሀገራችን አንደራደርም ከሰራዊቱ ጎን በመቆም ከስንቅ ማቀበል ጎን በጦርነቱ መሰለፍና መተኮስ መቻላችን ለጠላቶቻችን እናሳያቸዋለን ብለዋል፡፡
 
ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ከሰራዊቱ ጎን ነን ያሉት ወይዘሮዋ÷ ለኢትዮጵ የሚከፈለውን ሁሉ መስዋዕትነት ለመወጣት በቁርጠኝነትና በዝግጅት ላይ መሆናችን ለማሳየት ሰልፍ ወጥተናል በማለት ገልጸዋል፡፡
 
ሌላኛዋ የሰልፉ ተሳታፊ ወይዘሮ ሰርካለም በበኩላቸው÷ እኔ የወታደር ቤተሰብ ነኝ፤ 3 ወንድሞቼ በግንባር ላይ ጠላትን እየተፋለሙ ነው ፤እኔም ከስንቅ ማቀበል ጎን እዘምታለሁ፤ የሸዋ ሴቶች ተነሱ ጠላትን እዚሁ ሸዋ ላይ እንቅበረው ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
 
ከሰልፉ ጎን ለጎን የአዲስ አበባ የባህል ማዕከል የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ወቅቱን የሚመጥን የኪነ ጥበብ ዝግጅቶችን በማቅረብ የማነቃቂያና የንቅናቄ ዘመቻ መርሃ ግብር ማድረጋቸውን ከሰሜን ሸዋ ዞን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
አዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.