Fana: At a Speed of Life!

የደብረ ብርሃን ፋና ኤፍ ኤም 94.0 ሰራተኞች የዘማች አርሶ አደሮችን ሰብል ሰበሰቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደብረ ብርሃን ፋና ኤፍ ኤም 94.0 ሰራተኞች የዘማች አርሶ አደር ቤተሰቦችን የደረሰ ሰብል ሰበሰቡ።
 
ሰራተኞቹ በሰሜን ሸዋ ዞን ሞረትና ጅሩ ወረዳ በመገኘት ነው የዘማች አርሶ አደር ቤተሰቦችን የደረሰ ሰብል የሰበሰቡት፡፡
 
በሰላሙ ወቅት አራሽ የሆኑ በርካታ አርሶ አደሮች አሁን የሀገርን ዳር ድንበር ለማስከበርና ለነፃነት መዝመታቸውን ያነሱት ሰራተኞቹ÷ ወቅቱ አዝመራቸው የሚሰበሰብበት በመሆኑ ደጀን የሆነው ህዝብ ይህን ስራ አጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
 
ሰብላቸው የተሰበሰበላቸው ወይዘሮ አለም ተክሌ እና አቶ ተሾመ ነገሰ በበኩላቸው÷ህዝቡ ለዘማች ቤተሰብ እያደረገ ያለው ድጋፍ እኛን የሚያበረታ ዘማቾችንም ለበለጠ ድል የሚያነሳሳ ነው ብለዋል።
 
ስፍራው ድረስ በመገኘት የደረሰ ሰብላቸውን በመሰብሰብ ለተሳተፉት ሰራተኞችም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
የደብረ ብርሃን ፋና ኤፍ ኤም 94.0 ሰራተኞች ለህልውና ዘመቻው በሙያቸው ከሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ባለፈ የወር ደሞዛቸውን ለመከላከያ ሰራዊት በማበርከት እና ደም በመለገስ መሳተፋቸው የሚታወስ ነው፡፡
 
በአበበ የሽዋሉዕል
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.