Fana: At a Speed of Life!

የደጀንነት ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን – የደሴ ከተማ ነጋዴዎች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፀጥታ ኃይሎች በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ላይ በመውሰድ ላይ ያሉትን እርምጃ በመደገፍ ደጀንነታቸውን አጠናክረው መቀጠላቸውን የደሴ ከተማ ነጋዴዎች አስታወቁ፡፡
ነጋዴዎቹ ለኢዜአ እንደተናገሩት፥ የሀገር ህልውና ለማስጠበቅ ለዘመቱት ኃይሎች ድጋፍ እያደረጉ የንግድ እንቅስቃሴያቸውንም እያከናወኑ ናቸው።
በከተማው በንግድ ሥራ የተሰማሩት አቶ ጀማል አወል÷ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በለመደው የውሸት ወሬ ማፈናቀልና መዝረፍ እንደማይችል ይገልጻሉ።
አሸባሪ ቡድኑ ደሴን ተቆጣጥሬያለሁ ካለ ሳምንት ቢያስቆጥርም÷ እኛ በተረጋጋ ሁኔታ ሥራችንን እያከናወንን ወሎ መቀበሪያው እንዲሆን በቅንጅት እየሰራን ነው ብለዋል፡፡
ለጀግናው መከላከያ ሠራዊትና ሌሎች የጸጥታ ኃይሎች በተሰባሰበ ገንዘብ ውሃ፣ ደረቅ ስንቅና ሌሎች ግብዓቶች በማቅረብ ደጀንነታችንን በማሳየት ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡
በሽብር ቡድኑ የውሸት ወሬ ተደናግጠው ሱቆቻቸውን የዘጉት እንዲከፍቱ በማድረግ የከተማዋ የንግድ እንቅስቃሴ እንዳይቀዛቀዝ የድርሻቸውን እየተወጡ መሆኑንም ተናግረዋል።
ሥራችንን እያከናወንን ደጀንነታችንን ማጠናከር የህልውና ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡
ከተማችንንና ንብረታችንን ትተን የትም አንሄድም፤ የመጨረሻውን ድል እስከምናስመዝግብ ድረስም ሁለንተናዊ ተሳትፏችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ነው ያሉት፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.