Fana: At a Speed of Life!

የደ/ወሎ ዞን ቴክኒክና ሙያ ኢንተርኘራይዞች ልማት መምሪያ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ለህልውና ዘመቻ ድጋፍ አድርጓል

አዲስ አበባ፣መስከረም 21፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የደቡብ ወሎ ዞን ቴክኒክና ሙያ ኢንተርኘራይዞች ልማት መምሪያ እሰከ አሁን ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ለህልውና ዘመቻው ድጋፍ ማድረጉ ተገለፀ፡፡

የመምሪያው ሀላፊ አቶ መስፍን መኮነን ለፋና ብሮድካስንቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት ÷የአሸባሪውን ቡድን የጥፋት ተልዕኮ ለማክሸፍ ግንባር ድረስ በመዝለቅ ከሚፋለሙ የተቋሙ ሰራተኞች ባሻገር እሰከ አሁን ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ለህልውና ዘመቻው ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል።

ተቋሙ ለተፈናቃዮችም የአልባሳት ድጋፍ ማድረጉን የገለጹት ሀላፊው የሽብር ቡድኑ የህልውና ስጋት መሆን እሰከማይችልበት ደረጃ ድረስ ድጋፉ ይቀጥላል ብለዋል።

በከድር መሀመድ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.