Fana: At a Speed of Life!

የዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀክት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በተያዘላቸው እቅድ መሰረት እየተከናወኑ ነው – ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በበላይነት የሚመራውና በዓለም ባንክ የሚደገፈው የዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀክት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በተያዘላቸው እቅድ መሰረት እየተከናወኑ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዋ ሁሪያ አሊ ገለጹ፡፡
 
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ በዓለም ባንከ የኢትዮጵያን የዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀክት በበላይነት ከሚከታተሉት የድርጅቱ የአይ ሲ ቲ ፖሊሲ መሪ ዶክተር ቲሞቲ ኬሊ ጋር በፕሮጀክቱ አፈጻጸም ዙሪያ ዛሬ መክረዋል፡፡
 
ባለፉት 6 ወራት የተከናወኑ ስራዎችን ያብራሩት ሚኒስትር ዴኤታዋ ÷ ፕሮጀክቱ የታለመለትን ግብ እንዲመታና በኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ መሰረት ለመጣል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
በዓለም ባንክ የአይ ሲ ቲ ፖሊሲ መሪ እና በባንኩ የኢትዮጵያን የዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀክት የሚከታተሉት ዶክተር ቲሞቲ ኬሊ የዲጂታል ዘርፉን የሚደግፉ ቀጣይ ቀጠናዊ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን አንስተዋል፡፡
 
ኢትዮጵያም በእነዚህ ፕሮጀክቶች ተጠቃሚ መሆን እንደምትፈልግ ሚኒስትር ዴኤታዋ ማብራራታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
በቀጣይ ይፋ የሚደረገው አንዱ ቀጠናዊ ፕሮጀክት ኢትዮጵያን፣ ሱዳንን፣ ደቡብ ሱዳንንና ሶማሊያን ተጠቃሚ ማድረግ የሚችል ነው ብለዋል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.