Fana: At a Speed of Life!

የድህረ-ኮቪድ ገበያ ለማምረቻው ዘርፍ እንደ ምቹ አጋጣሚ ሊቆጠር እንደሚችል ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የድህረ- ኮቪድ ገበያ ለማምረቻው ዘርፍ እንደ ምቹ አጋጣሚ ሊቆጠር እንደሚችል የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ መከሰቱን ተከትሎ ክፉኛ ከተጎዱ ዘርፎች ወስጥ አንዱ የማምረቻው ዘርፍ ነው ተብሏል፡፡

ይህንን ዘርፍ ካጋጠመው መቀዛቀዝ ለማነቃቃት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተለያዩ የድጋፍ ማዕቀፎችን ዘርግቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ተካ ገብረእየሱስ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ ከዚህ በፊት ያልተለመደ እና ውጤትን መሠረት ያደረገ የማበረታቻ ስልት ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑን ሚኒስትር ዲኤታው  ተናግረዋል።

ይህም ስልት በዘርፉ የተሰማሩ ባለሃብቶች ስራቸውን በጥሩ ስነ ምግባር እንዲከውኑ ከማድረግ በዘለለ በባለሃብቶች መካከል ጤናማ የውድድር መንፈስ እንዲፈጠር ያደርጋልም ነው ያሉት፡፡

በቀጣይም ከድህረ-ኮቪድ በኋላ ዘርፉ የተራበ ገበያ ስለሚያገኝ ይህም ለዘርፉ ዳግም ትንሳኤ ሊሆን እንደሚችልና ባለሃብቶችም ይህንኑ እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው ምርታቸውን ወደ ተለያዩ የዓለም ሀገራት በመላክ ራሳቸውን ብሎም ሀገራቸውን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ማሳሰባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.