Fana: At a Speed of Life!

የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ላይ ጉድለት በተገኘባቸው የምርጫ ክልሎች የድምጽ መስጫ ቀን ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ የምርጫ ክልሎች የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ላይ ጉድለቶች መገኘታቸውን ተከትሎ ጉድለት የተገኘባቸው የምርጫ ክልሎች የድምጽ መስጫ ቀን መራዘሙን የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ቦርዱ 11 ቀናት በቀሩት ምርጫ ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል።

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ÷ ክፍተት ከተገኘባቸው የምርጫ ክልሎች የጸጥታ ችግር አለባቸው ተብለው ሰኔ 14 ድምጽ ከማይሰጥባቸው የምርጫ ክልሎች ጋር ድምጽ ይሰጥባቸዋል ብለዋል።

የቦርዱ የኦዲት ክፍል ባካሄደው ማጣራትም በ54 ምርጫ ክልሎች ላይ ክፍተት ተገኝቷል።

2ኛው የምርጫ ቀን ጳጉሜን 1 2013 ዓ.ም ይሆናል ተብሏል።

በምስክር ስናፍቅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.