Fana: At a Speed of Life!

የድሬደዋ ከተማ ግንባታቸው የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ግንባታቸው የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን አስመረቀ፡፡
 
በአስተዳደሩ በ2012 በጀት ዓመት ስራቸው የተጠናቀቁ የካፒታል ልማት ፕሮጀክቶች የምረቃ ስነስርዓት ተካሂዷል፡፡
 
በኢንዱስትሪ መንደር የተገነባው የመሬት ልማት ቢሮ ከ64 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ባለሦስት ወለል ህንፆ፣ የጎሮ ጤና ጣቢያ ደረጃ ማሳደግና የጎሮ 1 ደረጃ ትምህርት ቤት የማስፋፊያ ስራዎች ተመርቀዋል።
 
ለተለያዩ የመንግስት ስራ የሚውሉ 40 ፒክአኘ መኪናዎች ፣ 2 የእሳት አደጋ መኪናዎች ፣ 2 የውሀ መጓጓዥ ቦቴዎች ፣10 የደረቅ ቆሻሻ መኪኖች 4 የስጋ ማመላለሻ መኪኖች ለአገልግሎት ዝግጁ ተደርገዋል፡፡
 
መኪኖቹ ከ148 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሆነባቸው ናቸው።
 
በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር እየጨመረ የመጣውን የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ተቋማት የስራ ቦታ ችግር በመቅረፍ ውጤታማነታቸውን ለማሳደግ ቀድሞ ከነበሩት የማምረቻና የመሸጫ ቦታዋች በተጨማሪም የፈረስ መጋላ የገበያ መአከል ተመርቋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.