Fana: At a Speed of Life!

የድሬዳዋ ሆቴሎች ለዳያስፖራዎች የ30 በመቶ ቅናሽ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አገራዊ ጥሪውን ተከትለው ወደ አገር ቤት የሚገቡ ዳያስፖራዎችን ለማስተናገድ መዘጋጀቱን የድሬዳዋ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

ይህንኑ ዓላማ ታሳቢ ያደረገ የምክክር መድረክ ዛሬ በከተማዋ ከሚገኙ የሆቴል ባለንብረቶች ጋር ተካሂዷል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ ኢንዱስትሪና አንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ አብዲ ሙክታር በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት፥ ድሬዳዋ ዳያስፖራዎቿን ለመቀበል ተዘጋጅታለች።

አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንግዶችን በመቀበልና የቆይታ ጊዜያቸውን ለማራዘም የአገልግሎት አሰጣጣቸውን በማሻሻል እየሰሩ እንደሆነም ጠቁመዋል።

ከሆቴል ባለንብረቶቹ ጋር በነበረው ውይይትም ሆቴሎቹ የ30 በመቶ ቅናሽ ለማድረግ የተስማሙ ሲሆን ÷ አንድ ሆቴል ደግሞ ለእንግዶቹ የ50 በመቶ ቅናሽ በማድረግ መስተንግዶ ለመስጠት መዘጋጀቱ ተገልጿል።

1 ሺህ የሚጠጉ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አገራዊ ጥሪውን ተከትሎ ወደ ድሬዳዋ ይገባሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ፥ አስተዳደሩ በሚያዘጋጃቸው የተለያዩ የኢንቨስትመት አማራጮች መመልከቻ መድረኮች ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በእዮናዳብ አንዱዓለም

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.