Fana: At a Speed of Life!

የድሮን ቴክኖሎጂን በትብብር በማልማት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች መጠቀም የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሮን ቴክኖሎጂን በትብብር በማልማት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች መጠቀም የሚያስችል ከባቢያዊ ሁኔታ ለመፍጠር ያለመ ስምምነት ተፈርሟል።
ስምምነቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የቴክኖሎጂ ማሻሻያ፣ አስተዳደርና ድጋፍ ዘርፍ ሚኒስቴር ዲኤታ ዶክተር ያኒያ ሰኢድመኪ እና በዘርፉ የሚሰሩ ባለድርሻ እና አጋር አካላት ፈርመውታል።
እንደ ዶክተር ያኒያ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በቴክኖሎጂ ሽግግርና ልማት የግሉን ሴክተር ለማብቃትና አገራዊ ኢኮኖሚን ለማገዝ ድጋፍ ያደርጋል።
እስካሁን በቴክኖሎጂ ዘርፍ ድጋፍ እያደረገላቸውና በትብብር ከሚሰራባቸው ዘርፎች አንዱ የድሮን ቴክኖሎጂ ነው ብለዋል።
በዘርፉ ከፍተኛ ፍላጎት አዳጊ አቅም እየታየ ነው ያሉት ዶክተር ያኒያ÷ የድሮን ቴክኖሎጂ በግሉ ኢንዱስትሪ እና በማህበራዊ አገልግሎት ጥቅም ላይ እንዲውል የተደረጉ ድጋፎች ውጤት ማሳየት ጀምረዋልም ነው ያሉት።
አሁን በዘርፉ ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ሰፊ ፍላጎት እየመጣ የአገልግሎቱ ፈላጊም እየጨመረ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል ብለዋል።
መንግስትም ዘርፉ በሕግና በአሰራር ተደግፎ ጥቅም ላይ መዋል እንዳለበት ያምናል÷ ይህን ለማድረግ በርካታ ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛሉ ሲሉ ገልጸዋል።
የተፈረመው የስምምነት ወደፊት ቴክኖሎጂው ለልማትና ለማህበራዊ አገልግሎት እንዴት መጠቀም እንዳለብንና መሟላት ስላለባቸው ቅድመሁኔታዎች፣ የአጋር እና የባለ ድርሻ አካላት ሚና ለመለየትና ከመንግስት፣ ከተጠቃሚዎች፣ ከግሉ የቴክኖሎጂው ባለቤቶች ጋር በትብብር ለመስራት ምን እንደሚጠበቅ የተለየበት ነውም ነው ያሉት።
የፊርማ ስነስርዓቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው÷ የዚህ ዓይነት ወጥ አሰራርና የትብብር ማዕቀፍ ለመፍጠር የሚያስችል የትብብር ማዕቀፍ መጀመሩ ቴክኖሎጂውን ለመጠቀም፣ ለማሻሻልና በዘርፉ ለመስራት መነሳሳት ይፈጥርልናል ብለዋል።
በድሮን ቴክኖሎጂ ካሁን ቀደም በተበታተነ መልኩም ቢሆን የነበሩ እንቅስቃሴዎች በዘርፉ እምቅ አቅም እንዳለ አሳይቷል ያሉት ተሳታፊዎቹ÷ ቴክኖሎጂውን በውስጥ አቅም መጠቀም መቻል ለጥናትና ምርምር ከሚፈጥረው እድል ባሻገር ከውጭ ባለሃብትና ቴክኖሎጂው ባለቤቶች ጋርም ተቀናጅቶ ለመስራት ያስችላል ብለዋል።
መሰል መድረኮችና የአሰራር ማዕቀፎች ለመፍጠር የሚያስችል ምቹ ከባቢያዊ ሁኔታ ላይ የሚደረጉ የባለድርሻ አካላት እና የዘርፉ ተዋንያን ግንኙነቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል መባሉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.