Fana: At a Speed of Life!

የዶንባስ ግዛት ሙሉ በሙሉ በሩሲያ ወታደራዊ ኃይሎች ቁጥጥር ስር ዋለች

አዲስ አበባ፣ሰኔ 26፣2014( ኤፍ ቢሲ) የዶንባስ ሪፐብሊክ ሙሉ በሙሉ ከዩክሬን ጦር እጅ ወጥታ በሩሲያ ወታደራዊ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋሏን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾይጉ ለፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዛሬው እለት ባደረጉት ገለፃ የተራረፉ የዩክሬን ወታደሮች ከሉሀነስክ ህዝባዊ ሪፐብሊክ ግዛት ተጠራርገው መውጣታቸውን ነው ያስታወቁት፡፡
የሩሲያ ወታደራዊ ኃይሎች እና የዶንባስ ተገንጣዮች፥ ከ2014 ጀምሮ በዩክሬን ቁጥጥር ስር የቆየችውን የሉሀነስክ ክልል ዋና ከተማ ሊሲቻንስክን በዛሬው ዕለት ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ስለማዋላቸውም የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ለፕሬዚዳንት ፑቲን አስረድተዋል፡፡
የሩሲያ እና የዩክሬን ተፋላሚዎች በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የሊሲቻንስክ ከተማን ለመያዝ በከተማዋ የነዳጅ ማጣሪያ አካባቢ ከባድ ውጊያ ስለማድረጋቸው ቀደም ሲል ተዘግቧል፡፡
የሊሲቻንስክ ከተማ የተያዘቸው የዩክሬን ወታደራዊ ኃይሎች ከወራት ውጊያ በኋላ ከተያዘችበት ከሴቬሮዶኔስክ ከተማ አፈግፍገው ከወጡ ከአንድ ሳምንት በኋላ መሆኑም ተዘግቧል፡፡
የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ ቀደም ሲል በሩሲያ ወታደራዊ ኃይሎች የተያዙ ከተሞችን መልሰን እናስለቅቃለን ማለታቸው የሚታወስ ነው፡፡
ሩስያ በዩክሬን ወታደራዊ ዘመቻ ካደረገችበት ምክንያት አንዱ፥ ዩክሬን የሚንስክ ስምምነት መሠረት ዶኔስክ እና ሉጋንስክ የተሰኙትን ክልሎች የልዩ ራስ ገዝ አስተዳደር ለመተግበር ፈቃደኛ ባለመሆኗ እንደሆነ ስትገልጽ መቆየቷን አርቲ በዘገባው አመላክቷል።
የሚንስክ ስምምነት የተፈረመው በፈረንጆቹ 2014 በጀርመንና በፈረንሳይ አሻማጋነት እንደነበርም ይታወሳል።
ከስምምነቱ በኋላ የቀድሞው የዩክሬን ፕሬዚዳንት ፔትሮ ፖሮሸንኮ በሰጡት አስተያየት፥ የኬቭ ዋና ዓላማ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ለጊዜ መግዥያ በመጠቀም የዩክሬንን “ጠንካራ የጦር ኃይል ለመፍጠር ነው” ብለው ነበር።
ክሬምሊን በበኩሏ፥ በዚህ ዓመት የካቲት ወር ላይ የዶንባስ ሪፐብሊኮች ነፃ መንግስታት መሆናቸውን እውቅና መስጠቷን በማሳወቅ፥ ዩክሬንም በጉዳዩ ጣልቃ ከመግባት ራሷን እንደታርቅ እና የትኛውንም የአውሮፓ ወታደራዊ ማህበር እንዳትቀላቀል መጠየቋ የሚታወስ ነው።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.