Fana: At a Speed of Life!

የጁንታውን ቡድን እኩይ አላማ በማክሸፉ ሂደት አየር ሀይሉ የምድር ጦሩን ፈጣን ንቅናቄ በማሳለጥ በኩል የአንበሳውን ድርሻ ተወጥቷል-ሜ/ጀ ይልማ መርዳሳ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አየር ሀይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄነራል ይልማ መርዳሳ ፣ የጁንታውን ቡድን እኩይ አላማ በማክሸፉ ሂደት አየር ሀይሉ የምድር ጦሩን ፈጣን ንቅናቄ በማሳለጥ በኩል የአንበሳውን ድርሻ መወጣቱን አስታወቁ ።
ከማዕከል ወደ ግዳጅ ቀጠና የሚንቀሳቀስ ሎጅስቲክስ እና የሰው ሀይልን በወቅቱ በሚፈለገው ቦታ ማድረሳቸውን ያስታወሱት ዋና አዛዡ ÷ ሴረኛውን ቡድን በመደምሰሱ ሂደት የከፍተኛ አመራሩ መናበብ እና ቅንጅት ከፍተኛ እንደነበር ገልፀዋል።
አየር ሀይሉ የጦር ቁስለኞችን በወቅቱ የተሻለ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ከፍተኛ ስራ መስራቱን ጠቁመው ÷ የህክምና ቁሳቁሶችን እና መድሀኒቶችን በፍጥነት ለሰራዊቱ ያደርስ እንደነበር አብራርተዋል ።
የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያም የጤናውን ዘርፍ ተደራሽነት ለማረጋገጥ ከሌሎች አካላት ጋር የነበረው መናበብ እና የሚሰጣቸው ፈጣን ውሳኔዎች የሚደነቅ መሆኑን ሜጀር ጄነራል ይልማ መርዳሳ መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.