Fana: At a Speed of Life!

የጁንታውን ታጣቂ ሃይል በመምራትና በማዋጋት የተሳተፉት ሜጀር ጄኔራል መሐመድ እሻ እና ብርጋዴር ጄኔራል ሙሉጌታ በርሄ እጃቸውን ሰጡ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሰራዊት አባላት የነበሩትና በጡረታ በክብር የተሰናበቱት ሜጀር ጄኔራል መሐመድ እሻ እና ብርጋዴር ጄኔራል ሙሉጌታ በርሄ እጃቸውን በሰላም መስጠታቸውን የሃገር መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ።

የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ እጃቸውን የሰጡት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የጁንታውን ታጣቂ ሃይል በመምራትና በማዋጋት ላይ የነበሩ ናቸው።

መኮንኖቹ በጡረታ ከተገለሉ በኋላ ጁንታውን በመቀላቀል የጦርነት ዝግጅት ሲያደርጉ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

የሃገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ ላይ የህወሓት ጁንታ ጥቃት በፈጸመበት ወቅትም ዋና አስተባባሪ የነበሩ ናቸው።

አያይዘውም አሁን ላይ በርካታ የጽንፈኛው ቡድን ሚሊሻ ፣ ልዩ ሀይል እና የፖሊስ አባላት እጃቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉም ብለዋል፡፡

እጃቸውን የሰጡ አባላትም በአግባቡ ህጋዊ ከለላ እየተሰጣቸው ወደ ህብረተሰቡ ለመቀላቀል በዝግጅት ላይ ይገኛሉ ም ነው ያሉት፡፡

ቀሪዎችም ጁንታው በማይወክላቸው ጦርነት ውስጥ የሚማግዳቸው ሀይሎች ይህንን ዕድል ተጠቅመው እጃቸውን ለመስጠት ፍላጎት ካሳዩ አሁንም በሩ ክፍት መሆኑን አረጋግጠዋል ፡፡

ሠራዊቱም ወንጀለኞችን የማሰስና የማደኑን ተግባር አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፥ በየጊዜው ቦታ እየቀያየሩ ከሚደበቁበት ዋሻ ውስጥ እየተለቀሙ በቁጥጥር ስር እስከሚውሉ ድረስ አደኑ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስረድተዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.