Fana: At a Speed of Life!

የጁንታው መሪዎች መያዝ በትግራይ ውስጥ ተስፋን አንግሷል – አቶ ነብዩ ስሁል

አዲስ አበባ ፣ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የጁንታው መሪዎች መያዝ በትግራይ ውስጥ ተስፋ ማንገሱን አቶ ነብዩ ስሁል የትግራይ ክልል ብልፅግና ፅህፈት ቤት ኃላፊ ገለጹ።
የትግራይ ህዝብ ለዓመታት ስርዓቱ የሚገረሰስ በማይመስል ደረጃ ትልቅ ፕሮፖጋንዳ እየተነዛበትና አፈና እየተጫነበት መኖሩንም ነው ያመለከቱት
የጁንታው አመራሮች እና ስትራቴጂስቶች መያዝ ለትግራይ ህዝብ ትልቅ የነፃነት ተስፋ ያነገሰ መሆኑን ገልጸዋል።
በእርግጥ ከነበረው ፕሮፖጋንዳ አንፃር ነገሮችን ለማመን የተቸገረ ሰው ብዛት ቀላል ባይሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ በተለይም የጁንታው አመራሮች መያዝ ለውጡን በሙሉ ልብ ወደ መቀበሉ እየሄደ እንዳለ የሚያመላክቱ ማሳያዎች እየበዙ መጥተዋል ብለዋል።
የህውሓት አጥፊ ቡድን መሪዎች መያዝ መጀመራቸው ብዙ መልዕክት እንዳለው ያመለከቱት ሃላፊው÷ በዋነኛነት ከህግ አንፃር ሊጠቀስ የሚችለው ማንኛውም እና በየትኛውም ደረጃ ላይ ያለ ሰው ህግ ቢጥስ እና ቢያጠፋ በህግ ፊት የሚቀርብ እና ጊዜ ጠብቆ ተጠያቂነቱ የማይቀር መሆኑን የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ለትግራይ ህዝብ በተለይ ለወጣቱ የለውጥ ምዕራፍ ወለል ብሎ መከፈት መጀመሩን ያበሰረ ነው ማለታቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.